Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀሪያ የተመድ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር  ነብያት ጌታቸው በአልጀሪያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስተባባሪ ከሆኑት አምባሳደር ኤሪክ ኦቨረስት ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ነብያት ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በተጀመረው መልኩ እንዲቀጥል ፍላጎት ያላት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ ችግርን በተመለከተም ኢትዮጵያ በውይይት ለመፍታት የጸና አቋም አላት ብለዋል

አያይዘውም በትግራይ ክልል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን ለመርዳት በመንግስት እየተደረገ ስላለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት  ለአምባሳደሩ ገለጻ ማድረጋቸውን አልጀሪያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.