Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከህንድና ኮንጎ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጄሪያ ከህንድና ከዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ነብያት የወቅቱ የተመድ ተለዋጭ አባል ሀገር ከሆነችው የህንድ አምባሳደር ጎራቪ አህሉዋል እንዲሁም በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ኃላፊነትን ከተረከበችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ አምባሳደር ሮዝ ኦሳኩ ጋር በሁለትዮሽና አህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ ባለው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የድርድር ሂደት ላይ ያላትን ቁርጠኛ አቋም፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ውዝግብ ዙሪያ እንዲሁም መንግስት በትግራይ ክልል እያደረገ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.