Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከስዊዘርላንድና ከኢንዶኔዥያ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተቀማጭነታቸውን በአልጀርስ ካደረጉ ከስዊዘርላንድ አምባሳደር ሉካስ ሮዘን እና ከኢንዶኔዥያ አምባሳደር ቻሊፍ አክባር ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱም የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ ጉዳዮችና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከተ መሆኑ ተመላክቷል።
በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ነብያት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታና የሶስትዮሽ ድርድርን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ያሉትን አለመግባባቶችና ስጋቶች በውይይት ለመፍታትና ሁሉንም ፍላጎት ያካተተ መፍትሔ እንዲመጣ ያላትን አቋም ገልጸዋል።
ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ መሰረት በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የተጀመረው የድርድር ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በኢትዮጵያ በኩል ሙሉ ቁርጠኝነት ያለ መሆኑን ለዳይሬክተር ጄኔራሉ አስረድተዋል።
በተያያዘም የሁለተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት በመጪው የዝናብ ወቅት እንደሚካሄድ ገልጸውላቸዋል።
በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልከቶ እርዳታ ለሚስፈልጋቸው ዜጎች በመንግስትና በአጋር አካላት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን ፣ ለሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ሚዲያ ተቋማት ያልተገደበ ፈቃድ መሰጠቱን፣ ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተገናኘ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የጋራ ምርመራ ለማድረግ መንግስት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።
የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ውዝግብ በተመለከተ ሱዳን ዓለም አቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር ጥሳ መግባቷን ገልጸው ÷ችግሩን በፈረንጆቹ በ1972ቱ የሰነድ ልውውጥ መሰረት ባደረገ መልኩና በሁለቱ ሀገራት በተመሰረተው የጋራ የድንበር ኮሚሽን በኩል በውይይት እንዲፈታ በኢትዮጵያ በኩል ያለውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸዋል።
በቀጣይ ስለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ስኬታማ ለማድረግ በመንግስት በኩል ያለውን ቁርጠኝነትና እየተደረጉ ያሉ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል።
ባለፉት ሶስት አመታት በኢትዮጵያ በነበረው የለውጥ ሂደት በተወሰዱ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችና በተደረጉ የህግ ማሻሻያዎች ነጻና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ ማቋቋም መቻሉን አምባሳደሩ መግለጻቸውን አልጀሪያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
23
Engagements
Boost Post
23
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.