Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣሊያን የላይኛው ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ ከጣሊያን የላይኛው ምክር ቤት ሴኔት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፔትሮቼሊ ቪቶ ሮሳሪዮ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ዘነቡ በዚህ ወቅት የህወሓትን ቡድን በመመከላከያ ሰራዊቱ እና በጎረቤት ሃገር ኤርትራ ያደረገውን ትንኮሳ በዝርዝር በማስረዳት በተሰጠው በሳል አመራር የህግ ማስከበር ተግባር ተጠናቆ ለተፈናቀሉና ለተጎዱት ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ የማቅረብ እና መልሶ የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል ተቋርጠው የነበሩ እንደ ባንክ፣ ቴሌ፣ ውኃ እና መብራት የመሳሰሉ ማህበራዊ አገልግሎቶች መጀመራቸውን በመጥቀስ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ የመጠገንና ለአገልግሎት የማብቃት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አስረድተዋል።

የጣሊያን የላይኛው ምክር ቤት ሴኔት የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፔትሮቼሊ ቪቶ ሮሳሪዮ በበኩላቸው የኢትዮጵያና የጣሊያን ወዳጅነት ጠንካራና ታሪካዊ መሆኑንን አንስተዋል።

አያይዘውም የጣሊያን ፓርላማና የጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያ አሁን እያካሄደች ያለውን ለውጥ እንደሚደግፉ የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል በህወሓት ቡድን ላይ የወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ሙሉ በሙሉ የውስጥ ጉዳይ እና ማንም ጣልቃ ሊገባበት የማይችል መሆኑን አውስተዋል።

በዘመቻው ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ አስፈላጊ እንደሆነ እና በመንግሥታቸው በኩል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያን በቀጣይ ለመጎብኘትና በጋራ ጉዳዮች፤ በባህል፣ በልማት በንግድና ቱሪዝም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ትስስር በመፍጠር በጋራ ለመሥራት እንሚፈልጉ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.