Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከፈረንሳይ፣ ከህንድ እና ጃፓን አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከፈረንሳይ፣ ከህንድ እና ጃፓን አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል።

በሱዳን የኢፌዴሪ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከፈረንሳይ አምባሳደር ኢማኑኤሌ ብላትማን፣ ከህንድ አምባሳደር ራቪንድራ ፕራሳድ እና ከጃፓን አምባሳደር ታካሺ ሃቶሪ ጋር በወቅታዊ የሃገሪቱ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ይበልጣል በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ እየተደረገ ስላለው ዝግጅት ገለጻ አድርገዋል።

በተጨማሪም ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ የኢትዮጵያን አቋም በተመለከተ ማስረዳታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.