Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሱዳን የኢፌዲሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ዋና ጸሃፊ አምባሳደር መሃመድ ሸሪፍ አብደላህ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱም በትግራይ ክልል የተካሄደው ህግ ማስከበር ዘመቻመጠናቀቁን በመግለፅ፤ አሁን እየተከናወነ ያለው የህወሓት የጥፋት ቡድንን አድኖ ለህግ የማቅረብ፣ የማህበራዊ አገልግሎቶችን የማስጀመር፣ የጥፋት ቡድኑ ያፈራረሳቸውን የመሰረተ ልማት አውታሮችን ጠግኖ ወደ ስራ የማስገባት እንደሆነ አምባሳደር ይበልጣል አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በሱዳን የስደተኛ ካምፕ ከሲቪሉ ጋር የገቡ የህወሓት ወንጀለኞች ለዓለም አቀፍ ሚዲያ የተዛባ መረጃ እየሰጡ መሆኑንም አንስተዋል።

ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ዋና ጸሃፊ አምባሳደር መሃመድ ሸሪፍ አብደላህ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ እንደሚከታተሉ ገልፀዋል።

ችግሩ እንዲቋጭ ሱዳን የተቻላትን ድጋፍ ሁሉ እንደምታደርግ የገለፁ ሲሆን፥ ሲዳን ስደተኞችን ተቀብላ በማስተናገድ ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.