Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ በታንዛኒያ ከሱዳን ኤምባሲ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ መቀመጫውን ታንዛኒያ ካደረገው የሱዳን ኤምባሲ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የፌደራል መንግስት በክልሉ ህግ የማስከበር ስራ ለመስራት መገደዱን አስታውሰው ስለ ህግ ማስከበር ስራው ዝርዝር ሁኔታ ገለጻ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በተመለከተ በቅርቡ በድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ሁኔታ አንስተው ተወያይተዋል። በውይይቱም ሁለቱ ሃገራት ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማውሳት በሁለቱ ወንድማማች ሃገራት መካከል የሚከሰት ማንኛውም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ሊፈታ እንደሚገባ እና አላስፈላጊ ግጭቶችን በአፋጣኝ ማስወገድ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሱዳን ጉዳይ ፈጻሚ በበኩላቸው በትግራይ ክልል መንግስት የወሰደውን ህግ የማስከበር ዘመቻ በማስመልከተ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ አምባሳደሩ ለሰጧቸው ገለጻ አመስግነው ሁኔታውን መንግስት በቁጥጥር ስራ ማዋሉን አድንቀዋል፡፡

በቀጣይም ህዝቡ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ የተጀመረው ስራ በስኬት እንደሚጠናቀቅ እምነታቸውን ገልጸዋል።

የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት በተመለከተም የሃገራቱ የህዝብ ለህዝብ ትስስር የጠነከረ መሆኑን በማውሳት አሁን የተከሰተውን የድንበር ውዝግብ በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሁለቱንም ሃገራት ብሄራዊ ጥቅም የሚያስከብር ነው ማለታቸውን ከታንዛኒያ የኢትዮጵ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.