Fana: At a Speed of Life!

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይካድራ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች በስለት እንደተገደሉ ማረጋገጡን አስታወቀ።
የድርጅቱ በሳተላይት እና በቀውሶች መረጃ ላቦራቶሪ በተካሄደ ምርመራ በማይካድራ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሰዎች በየቦታው ተጥለው ወይንም ሰዎች በቃሬዛ አስክሬኖችን ተሸክመው ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ ምስል እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማግኘቱን ገልጿል።
የተገኙት እነዚህ ምስሎችም የቅርብ ጊዜያት እንደሆኑ ማረጋገጥ መቻሉን ድርጅቱ አስታውቋል።
በርካታ ሰላማዊ ዜጎች መጨፍጨፋቸውን አረጋግጫለሁ ያለው ድርጅቱ፤ በዚህ ጭፍጨፋ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች መንግስት በአካባቢው እየወሰደው ከሚገኘው ህግን የማስከበር እርምጃ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሰላማዊ ዜጎች መሆናቸውንም ገልጿል።
በርካታ አስክሬን የተገኘው በከተማዋ መሀል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ከተማዋን ከመቆጣጠራቸው በፊት ነው ብሏል አምነስቲ በመግለጫው።
ሰላማዊ ዜጎቹ የተገደሉት በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች መሆኑን ያስታወቀው አምነስቲ፤ ከአይን እማኞች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ግድያውን የፈፀሙት የህወሓት ቡድን የሚመራው የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት እና ሚሊሻዎች ናቸው ብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.