Fana: At a Speed of Life!

”አረንጓዴ አሻራ ቀጣይነት ላለው መማር ማስተማር ”በሚል መሪ ቃል በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ”አረንጓዴ አሻራ ቀጣይነት ላለው መማር ማስተማር፣ ምርምር፣ማህበረሰብ አገልግሎትና ገቢ ማመንጫ ”በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ኢላዳሌ እርሻ ጣቢያ ተካሄደ፡፡

እንደ ሀገር  የዘንድሮው  የአረንጓዴ  አሻራ ዘመቻ “ኢትዮጵያን እንላብሳት”  በሚል መርህ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲም በዛሬው ዕለት በግብርናና እንሳሳት ህክምና ኮሌጅ አስተባባሪነት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ በማሳተፍ 25 ሺህ የቡና ችግኖችን ተተክሏል፡፡

በተካላው ላይ የተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራችንን በማኖራችን ደስተኞች ነን ዛሬ የተከለው የቡና ችግኝ ለቀጣይ ትውልድ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈው የገቢ ምንጭ የሚሆን ጭምር ነው ብለዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ዲን ዶክተር ፍቃዱ ምትኩ ባለ አምስት ዝርያ  25 ሺህ  የቡና ችግኝ 70 ሄክታር ስፋት ባለው ኢላዳሌ እርሻ ጣቢያ መተከሉን ገልጸው÷ በዘመቻው አረንጓዴ አሻራን ከማሳረፍ ባለፈ ለመማር ማስተማር፣ምርምር፣ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ገቢ ማመንጫነት የሚሉ ናቸው  በመትከል ባለፈ እንዲፀድቁ ያልተቋረጠ እንክብካቤና ክትትል እናደርጋለን ሲሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ  ዩኒቨርሲቲው የአረንጓጌ አሻራ መርሃ- ግብርን ከተልዕኮው ጋር በተሰላስለና ዕውቀት በታከለበት ሳይንሳዊ መንገድ ተግባሪዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በአረንጓጌ አሻራ ከ150 ሺህ በላይ ችግኞችን መትከሉን ያስታወሱት ዶክተር ጀማል÷ በዘንድሮው ዘመቻ ከቡና ችግኝ በተጨማሪ  ከ100 ሺህ በላይ ሌሎች  ችግኞችን መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡

በተመስገን አለባቸው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.