Fana: At a Speed of Life!

አራት ትውልድ የሚጣመርበት ታላቅ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ድግስ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ)አራት ትውልድ የሚጣመርበት ታላቅ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ድግስ በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
የኪነጥበብን ሃያልነት በመጠቀም በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና” በቃ” ለማለት የሚያስችል የሙዚቃ ድግስ በመጪው ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ይከናወናል።
ይህን መርሃ ግብር የተመለከተዝርዝር መግለጫ በአንጋፋና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች ዛሬ ተሰጥቷል።
ከሙዚቃ ዝግጅቱ የሚገኘው ገቢ የተጎዱ ወገኖችን ለመደግፍ ይውላል ተብሏል።
ከዚያም ባለፈ ዝግጅቱ ኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚፈጥር፣ በኪነ ጥበብ ሃገራዊ ሃላፊነት መወጣት እንደሚቻል ለማሳየት መሆኑን በመግለጫው ተነስቷል።
ጥር 21 ቀን ከሚቀርበው የሙዚቃ ዝግጅት ባሻገር ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም በወዳጅነት አደባባይ መሰል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንደሚኖርም ተጠቁሟል።
የሙዚቃ ድግሱ ቲኬት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚሸጥ መሆኑን ነው አርቲስት ታማኝ በየነ በዚሁ ወቅት የገለጸው።
ኢትዮጵያዊያን በችግር ጊዜ አንድ የምንሆን፣ ተለያዩ ስንባል የምንጣመር ልዩነቶቻችን ውበታችን የሆንን ህዝቦች ነን ተብሏል በመግለጫው።
አንድነታችንን አጠናክረን የመጨረሻ መዳረሻችን ወደ ሆነው አሸናፊነት እንደርሳለንም ነው የተባለው።
በቆንጂት ዘውዴ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.