Fana: At a Speed of Life!

አርሲ ዩንቨርሲቲ በተለያየ መርሐ ግብር ያስተማራቸዉን 2 ሺ755 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬዉ እለት በዩንቨርሲቲዉ የማህበረሰብ ሳይንስና ሂዩማኒቲ ኮሌጅ በበቆጂ ካምፓስ በስምንት የትምህርት ክፍል በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 831 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

የኮሌጁ ዲን ዶክተር ዋቆ ገዳ በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ትልቅ ድል በተደላደለ ሁኔታ መጓዝ ሳይሆን ችግርን ተጋፍጦ ማለፍ ነው ብለዋል።

የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዱጉማ አዱኛ በብዙ ችግርና ፈተና ዉስጥ ስለተመረቃችሁ ጀግኖች ናችሁ ብለዋል።

ኮቪድን እና በሀገሪቱ ያለዉን የፀጥታ ሁኔታ እየተጋፈጡ መማር ማስተማሩ እንዲቀጥል ዋጋ እየከፈሉ ለሚገኙ የጤና ባለሞያዎች እና የመከላከያ ሰራዊትም ምስጋና  አቅርበዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳና የዩኒቨርስቲው ቦርድ አባል ፕሮፌሰር እንዳሻው በቀለ፥ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልክት ተመራቂዎቹ ያገኙትን ዕዉቀት እንዲገመግሙና እና ከበፊቱ የበለጠ ጊዜያቸዉን ተጠቅመዉ የሀገሪቱን ችግር መፍታት እንዳለባቸዉ አስገንዝበዋል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በክረምትና ቅዳሜና እሁድ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

በቅድስት ዘዉዱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.