Fana: At a Speed of Life!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ4 ሺህ 858 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ከ4 ሺ ህ858 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ ፣በሁለተኛ ድግሪና በሶስተኛ ድግሪ መርሃ ግብር በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁትን ነው ያስመረቀው፡፡

ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በዶክተሬት ዲግሪ አንድ ተመራቂ አስመርቋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያካበቱትን ልምድና እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸው ሊያበረክቱ እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ተናግረዋል፡፡

ሠላም ልማትንና ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ተመራቂዎች የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሶስተኛ ድግሪ ማስመረቁ የዘንድሮውን ምርቃት ለየት እንደሚያደርገው የገለፁት ዶክተር ዳምጠው፤ ይህም ለዩኒቨርሲቲው ምስረታ መነሻ ከሆነው ከውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ባደረጉት ንግግር በሃገሪቱ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራቱ ረገድ ሰፊ ሥራዎች እተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችም በሙሉ አቅማቸው ለሃገሪቱ እድገት እና ብልጽግና በሠለጠኑበት ሙያ በቁርጠኝነት ማገልገል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

ለሀገሪቱ ሠላምና አንድነት መጠናከር ተመራቂዎች የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ተመራቂዎቹ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ቀደም ሲል ካደረጉት የበለጠ ሥራ እንደሚጠብቃቸውም ተናግረዋል።

የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲው በ33 ዙር 61 ሺህ 817 ተመራቂዎችን አስመርቋል፡፡

በአበበች ኬሻሞ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.