Fana: At a Speed of Life!

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 87 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለሰባተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 87 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ፡፡

ከተመራቂዎች መካከል 32 ሴቶች ሲሆኑ፥ ተመራቂዎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኮቪድ-19 ለመከላከልና ለማከም በተሠራው ሥራ ከፍተኛ አስተዎዕኦ ማበርከታቸው ተነግሯል፡፡

በሀገሪቱ ለህብረተሰቡ ጤና መሻሻል በመንግስት በኩል እየተደረገ ለሚገኘው ርብርብ ስኬታማነት የተመራቂዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎችም በሙሉ አቅማቸው ለሃገሪቱ እድገትና ብልጽግና በሠለጠኑበት ሙያ በቁርጠኝነት ማገልገል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳና የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው በሃገሪቱ በጤና ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራቱ ረገድ ሰፊ ሥራዎች እተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተመራቂዎቹ የኮቪድ ወረርሽኝን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ቀደም ሲል ካደረጉት የበለጠ ሥራ እንደሚጠብቃቸውም አመላክተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የገበዩትን እውቀትና ክህሎት በላቀ ደረጃ መጠቀም ይገባቸዋልም ነው ያሉት፡፡

የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲው በሰባት ዙር 572 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል፡፡

በማቴዎስ ፈለቀ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.