Fana: At a Speed of Life!

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ልማት፣ በቢግ ዳታ ፣ በሮቦቲክስና አቅም ግንባታ ዙሪያ አብሮ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ስምምነቱ የኮሚሽኑን አገልግሎቶች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለማዘመን ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ÷ከማዕከሉ ጋር አብሮ በመስራት ኢትዮጵያ ወደ ብልፅግና የምታደርገውን ጉዞ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የመሰሉ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ማፋጠን እንደሚገባ መናገራቸውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.