Fana: At a Speed of Life!

አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አትሌቲክስ አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በ2019 በአትሌቲክሱ ዘርፍ የአመቱን ምርጦች ይፋ አድርጓል።

በአሰልጣኞች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል።

ከዚህ ባለፈም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች የአመቱ ምርጥ ወጣት አትሌት ዘርፍ አሸንፈዋል።

ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌይ ደግሞ በሴቶች የአመቱ ምርጥ አትሌት አሸናፊ ሆናለች።

ሌላኛው ኬንያዊ ቲሞቲ ቼሩዬት በወንዶች ምድብ የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አትሌት አሸናፊ ሆኗል።

ምንጭ፦ አፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.