Fana: At a Speed of Life!

አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር እንሰራለን -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ምህዳር እንዲኖር እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዘመናት የተከማቹ የመጡትን የኢኮኖሚ ችግሮች ለማሸነፍ በአንድነት መነሳት ይኖርብልም ነው ያሉት፡፡
የውስጥ ሽኩቻን እንዳይኖር በመነጋገርና በህብረ ብሄራዊነት አንድነት መስራት ይኖርብናል፥ ለዚህም ሁሉንም ሕብረተሰብ ክፍሎች ያካተተ የውይይት መድረኮች ይኖሩናል ብለዋል፡፡
ጠላት የሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ግፍ ፈጽሟል፣ ት/ቤት እና የጤና ተቋማትን እየዘረፈ ህጻናትና ንጹናንን ገድሏል ለዚህም በእብሪቱ ዋጋ አስከፍሎናል ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም ወደን ሳይሆን ተገደን ህልውና ወደ ማረጋገጥ የገባንበት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ይህም ከኢትዮጵያ ጠል ሀይሎች ጋር ብቻ የገባንበት የህግ ማስከበር ዘመቻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።
የተሟላ አቅም ያለው የጸጥታና ደህንነት ሀይል እንገነባለንም ነው ያሉት።
ከዲፕሎማሲ አንጻር የኢትዮጵያን ሎዓላዊነት ባከበረ መልኩ በፍቅር አብረውን ከሚሰሩት ጋር መድረኩ ሁሌም ክፍት ነው።
አንድ የተባበረች አህጉር እንዲኖረንም በአንድነት እና በፍቅር መስራት አለብን ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.