Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ ለኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ የበሬና የበግ ስጦታዎችን አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲከፋፈል አሰራጨ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ ከተለያዩ ባለሀብቶች የተሰበሰቡ የበሬና የበግ ስጦታዎችን አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲከፋፈሉ አሰራጨ፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ ባለሀብቶች ያሰባሰቧቸውን የእርድ በሬዎችን እና በጎችን በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በመገኘት አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በቅርጫ መልክ እንዲያከፋፍሉ ለወጣቶቹ አበርክተዋል።

ወጣቶቹም የተሰበሰቡትን 20 የእርድ በሬዎች እና ከ200 በላይ በጎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ሙስሊም አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የሚያከፋፍሉ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተመሳሳይ የፋሲካን በዓልን ምክንያት በማድረግ ከባለሀብቶች የተሰባሰቡ 40 በሬዎችን ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች እንዲከፋፍሉ ለተለያዩ አካባቢ ወጣቶች ማከፋፈላቸው እንደሚታወስ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.