Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደሩ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እና በባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት ለሚረዱ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በነገው እለት የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ነው አስተዳደሩ የእርድ እንስሳትን ያበረከተው።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ አብሮነታችን የአንድ ቀን ጉዳይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ነውና ዛሬም በበጎነት፣ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች በመኖር ምሳሌ ለመሆን ብንተጋ ሁላችንም የምንሰጠው አናጣም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.