Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት ተገዶም ቢሆን ሽንፈቱን እያመነ ነዉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት በሜካናይዝድ ኃይል የተደገፈ ጦሩ ጉዳት እያደረሰብን ስለሆነ ወደ ህገ መንግስታዊ ክልላችን ተመልሰናል ሲል የአሸባሪው ህወሓት ወታደራዊ አመራር የሆነው ጻድቃን ገብረትንሳይ የቡድኑን ሽንፈት በግድም ቢሆን ተቀብሏል።

ከቢቢሲ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረገው ፃድቃን ከሣምንታት በፊት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በወረራ በርካታ የአማራ ቦታዎችን እንደያዘና አዲስ አበባ ገብቶ ማዕከላዊውን መንግስት ለመቆጣጠር ጥቂት ቀናት ብቻ እንደሚያስፈልገው መግለጹን ዘገባው አስታውሷል፡፡

ሁሉንም የሰላም አማራጮች ረግጦ ጦርነት የከፈተውና የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሲያስተጋባ የነበረዉ ፃድቃን ሽንፈቱን እያጣጣመ ነዉ፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁኔታው ተቀልብሶ የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከባዶ ፉከራ ወደ መደምሰስ እና የተረፉት ወደ ትግራይ የመፈርጠጥ ሁኔታ ውስጥ መግባቱን ጠቁሟል፡፡

ቢቢሲ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሁኔታውን “እስትራቴጂያዊ ማፈግፈግ አድርገን ወደ ትግራይ ተመልሰናል” እያለ እንደሚገኝም አንስቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንደተደመሰሰ ከፊሉም እየፈረጠጠ እንደሚገኝ መጠቆሙን እና አሁን ላይ አሸባሪው የሠላም ጥሪ የሚያቀርበው ስለተሸነፈ ነው ማለቱንም ነው የጠቆመው፡፡

ጻድቃን፥ ወታደራዊ ኃይላቸውንና ሎጀስቲክ የጫኑባቸውን ተሽከርካሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት እንዳወደመባቸው አንስቶ ለመሸነፋቸው ምክንያት እንደሆነ ተናግሯል።

ጦርነቱ አልቋል፤ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ያለው ሰውዬ ሀይላቸው ትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኝ፣ የተንጠባጠቡ ኃይሎቹም ወደ ትግራይ እየተመለሱ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልጿል፡፡

መንግስት ያቀረባቸውን የሰላም አማራጮችን በሙሉ ግን ረግጦ ወደ ጦርነት መግባቱንም ዘንግቶም ለሰላም እድል ለመስጠት ነው የወጣነው ሲል ተደምጧል።

ሙሉ በሙሉ የተኩስ አቁም አድርገን ወደ ሠላማዊ ውይይት መግባት እንፈልጋለን ሲልም የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን አመራሮች ሽንፈት እና ተማጽኖ በቢቢሲ አሰምቷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.