Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በፈረንጆቹ 2013 ላይ 424 የአኝዋክ ብሄረሰብ አባላትን በግፍ ጨፍጭፏል – በአሜሪካ ሚኔሶታ ኦስቲን ም/ ቤት አባሉ ኦባላ ኦባላ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በፈረንጆቹ 2013 ላይ 424 የአኝዋክ ብሄረሰብ አባላትን በግፍ መጨፍጨፉን ትውልደ ኢትዮጵያዊው እና በአሜሪካ ሜኒሶታ ኦስቲን የምክር ቤት አባሉ ኦባላ ኦባላ ገለጸ፡፡
 
ኦባላ ኦባላ ከውጭ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቆይታ÷ ህወሓት በፈረንጆቹ 2013 ታህሳስ ወር ላይ በጋምቤላ ክልል ከሚገኙ አምስት ብሄረሰቦች ውስጥ አንዱ በሆነው አኝዋክ ብሄረሰብ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መፈጸሙን አስታውሷል፡፡
 
በዚህ በአሸባሪው ህወሓት በተጠነሰሰው የዘር ማጥፋት ድርጊትም 424 የሚደርሱ የአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት በግፍ መጨፍጨፋቸውን አንስቷል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም የሽብር ቡድኑ በጋምቤላ ከተማ ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ነው የገለጸው፡፡
 
ከጥቃቱ ለማምለጥም ወደ ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን በማቅናት ለ10 ዓመታት በስደተኝነት እንደቆየ አስረድቷል፡፡
 
በደቡብ ሱዳን በስደተኞች ጣቢያ በቆየባቸው ጊዜያቶችም በርካታ አስከፊ ችግሮችን እንዳሳለፈ አስታውሷል፡፡
 
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ኦባላ ኦባላ በቅርቡ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ በቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ዜጎችን ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን እንዳብራራላቸው ይታወሳል፡፡
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.