Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ወልዲያ በቆየባቸው ጊዜያት እጅግ አሰቃቂ ግፍ መፈጸሙን የዓይን እማኞች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን ወልዲያ በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት እጅግ አሰቃቂ ግፍ ሲፈጽም ቆይታል ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በከተማዋ ሴቶችን አስገድደው በመድፈር÷ ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ በመጨፍጨፍና ንብረት በማውደም ግፍ መፈጸማቸውን ነዋሪዎቹ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪ ቡድኑ ወደ ከተማዋ ከገባበት እለት ጀምሮ የሰቆቃ ጊዜ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች “በርካታ ወጣቶችን በአደባባይ በግፍ ገድለዋል፤ ሴቶችን በቡድን ደፍረዋል፤ የግለሰቦችን ቤት በየቀኑ እየፈተሹ ሃብት ንብረት ዘርፈዋል” ብለዋል፡፡
ወልድያ ሆስፒታል እና ዩኒቨርስቲን ጨምሮ የጤና ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶችና የፋይናንስ ተቋማት ሙሉ በሙሉ መዘረፋቸውንም ነው የገለጹት።
ኢትዮጵያውያን ወገኖች አዲስ ዓመትን ሲያሳልፉ እኛ በጨለማ ውስጥ ነበርን፤ ”የእኛ አዲስ ዓመታችንና ዳግም ውልደታችን ዛሬ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ÷ የሽብር ቡድኑ ለአዕምሮ የሚከብድ ወንጀል ፈጽሟልም ” ነው ያሉት፡፡
በከተማዋ በርካታ ወጣቶች በአደባባይ በግፍ መገደላቸውንም ገልጸው÷ የሽብር ቡድኑ መንገድ ላይ የሚለምኑ ሰዎችን ሳንቲም ጭምር በመውሰድ የነውረኝነቱን ጥግ አሳይቷል ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.