Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ያላከበረው የተኩስ አቁም መንግስት ለሰላም የሄደውን ርቀት የሚያሳይ ነው – አቶ ዛዲግ አብርሃ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ያላከበረው የመንግስት የተናጥል የተኩስ አቁም የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም የሄደውን ርቀት የሚያሳይ እንደሆነ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ከዶች ቬሌ “ኮንፍሊክት ዞን” ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ እንደተናገሩት፥ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላም ለማምጣት በሄደበት ርቀት አሸባሪው ቡድን ስምምነቱን ባለማክበር ህዝብ ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጥፋት እንዲደርስበት ማድረጉን አንስተዋል፡፡

በአማራ እና አፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎችን በመውረር ከሰው ህይወት ማጥፋት በተጨማሪ ሴቶችን መድፈሩን እና አርሶ አደሩን መዝረፉን እንዲሁም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተለያዩ ከተሞች ላይ ውድመት ማድረሱን አንስተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት በጠራው ስብሰባ ላይ ለምን እንደማትካፈል ለተጠየቁት ጥያቄ፥ ኢትዮጵያ በስብሰባው የማትካፈለው ብቸኛ አገር አለመሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

አክለውም አንድም አፍሪካዊ አገር በስብሰባው እንደማይካፈል እና ይህም አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰውን የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት መረዳታቸውን የሚያመላክት እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም የአገርን ሉዓላዊነት ባከበረ መልኩ እውነታውን እንዲመለከት የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀዱንም በቃለ መጠይቁ ላይ ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.