Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ያደረሰው ውድመት ኢትዮጰያን የማፍረስ የረጅም ጊዜ እቅድ እንደነበረው ያሰየ ነው – የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮች

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስልምና ጉዳይ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰበትን የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተመልክተዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳይ ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ሱልጧን አማን እንደገለጹት÷የሽብር ቡድኑ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን እንዳልሆኑ አድርጎ መዝረፉና ማውደሙ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለረጅም ጊዜ አቅዶ መስራቱን ያሳየ ነው፡፡
 
ተዘዋውረው የተመለከቱት ውድመትም ለማመን የሚከብድ፣ ዘግናኝ፣ ከሰው ልጅ ያውም ከወገን የማይጠበቅ አሳፋሪ የታሪክ ጠባሳ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
 
የተመለከትነውን ሁለተናዊ ጥፋት ለህብረተሰቡና ለአጋር አካላት በማሳየትና በማስረዳት ድጋፍ ለማድረግና በዘላቂነት ለማቋቋም የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ አብራርተዋል።
 
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸህ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው÷ የሽብር ቡድኑ ያደረሰውን ሁለተናዊ ጉዳት በወሬ ብንሰማም በዓይናችን ተመልክተን ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በስፍራው ተገኝተናል ብለዋል።
 
ህብረተሰቡን አስተባብረንም የወደመውን ገንብተን አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን፤ ከመንግስት ጎን ተሰልፈን የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግም ዝግጁ ነን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
የዓለም አቀፍ ታሪክ ጥናትና ምርምር ባለሙያ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ÷ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጠላቶቻችን ቢሰሩም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ እያከሸፈው ነው ብለዋል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ ያደረሰው ውድመትም በታሪክ ሰንዶ በመያዝ ትውልዱ እንዲማርበትና የሽብር ቡድኑ ሲያፍር እንዲኖር መደረግ እንዳለበትም አመልክተዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.