Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ሳማንታ ፓወር ተናገሩ

 

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 28፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ ቀደም ብለው በትግራይ ክልል ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ በተመለከተ ከሠላም ሚኒስትርና ከሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የሚቀርበው የሰብዓዊ ድጋፍ አሁንም መፋጠን እንዳለበት ጠቁመው በዚህም ከመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

ይሁንና በዚህ የሰብዓዊ ቀውስ ወቅት አሸባሪው ሕወሃት ወደ አጎራባች ክልሎች የሚያካሂደው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አንዳሳሰባቸው ነው ሃላፊዋ ሳማንታ ፓውር የተናገሩት።

በዚህ ሕወሃት በሚያደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል 150 ሺህ ሰዎች በአፋር ደግሞ 76 ሺህ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ነው ያረጋገጡት።

በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ላለፉት አራት ቀናት በሱዳን ጉብኝት አድርገዋል።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በተግባር በመንቀሳቀስ በአገር መከላከከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙን ጨምሮ በዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ:- ኢዜአ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.