Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ሸኔና ሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች የሰላም እና ደህንነታችን እንቅፋት ናቸው አሉ የምሥራቅ ወለጋ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሸኔ እና ፅንፈኛ ኃይሎች የሰላም እና ደህንነታችን እንቅፋት ናቸው ሲሉ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ አወገዙ።

በሺዎች የሚቆጠሩ የነቀምቴ ከተማ እና የዞኑ ነዋሪዎች በነቀምቴ ስታዲየም ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ፥ የአሸባሪው ሸኔን እና የፅንፈኛ ኃይሎችን የጥፋት ድርጊቶች በጋራ አውግዘዋል።

በአብሮነት የመኖር ባህላችንንና እሴቶቻችንን በመሽርሸር ለግል የፖለቲካ ፍጆታ እያዋሉ ሰላማችንን የሚነሱ አካላትን በአንድነት ለህግ እናቀርባለን ነው ያሉት የዞኑ ነዋሪዎች።

“ለየአከባቢያችን ሰላም በየራሰችን አስተዋፅኦ ኃላፊነታችንን እንወጣለን፤ በህዝብ ስም የሚዘርፉ እና የሰላም ጠንቅ የሆኑ አካላትን በጋራ እንታገላለን” ሲሉም ተደምጠዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የጥፋት ኃይሎችን መቃወሙ ለሰላም መስፈን ያለውን ፍላጎት ያረጋገጠበት እና የሰቆቃ ጊዜ ይብቃኝ ማለቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ቶሌራ ረጋሳ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዩብ ተካለኝ በበኩላቸው ፥ አሸባሪው ሸኔ አጥፊ እና የጥፋት ቡድኖች ተላላኪ በመሆን የህዝብን ሰላም ሲያደፈረስ መቆየቱን ተናግረዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ፥ የህዝብን ሰላም ለማስፈን የክልሉ መንግስት ከፌዴራል የፀጥታ አካለት ጋር በመሆን በሽብርተኛው ሸኔ እና በሌሎች ፅንፈኛ ኃይሎች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በማጠናከር የሰላም ማስከበር ስራው ይቀጥላል ብለዋል ።

በአፈወርቅ አለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.