Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን በሴቶችና ህፃናት ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለማስቆም መተባበር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የሐረሪ ክልል ሴቶችና ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአፋርና በአማራ ክልል በሴቶችና ህፃናት ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ ለማስቆም ተባብረን መስራት እንደሚገባ ገለጹ።

የክልሉ ሴቶችና ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ጋር በመሆን በአፋር እና በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ህጻናትና ሴቶች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክተዋል።

ድጋፉም በክልሉ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍል የተሰባሰበ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

ድጋፉን ያስረከቡት የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም እንደገለፁት÷ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአፋር እና በአማራ ክልል በሴቶችና ህፃናት ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ማፈናቀል ለማስቆም ተባብረን መስራት ይገባል።

በተለይም በዚህ ጦርነት ምክንያት በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በመጠቆም÷ ይህንን ችግር ለማቃለልም ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

ድጋፉ የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ እና የተለያዩ የሴት አደረጃጀት ጋር በጋራ በመሆን ከተለያዩ ማህበረሰብ ክፍል የተሰባሰበ መሆኑን አንስተው÷ በቀጣይ መሰል ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ መፍቱሃ አልዪ በበኩላቸው÷ የአሸባሪው ትህነግ ቡድን ሀገር የማፍረስ ሴራን በመመከት የሀገራችንን አዲስ ምዕራፍና የብልጽግና ጉዟችንን እናረጋግጣለን ሲሉ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.