Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የወጠነው ዕቅድ እንደማይሳካ በተግባር አሳይተነዋል-አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በእብሪት ተወጥሮ አፋር ክልልን እንደመሸጋገሪያ ድልድይ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የወጠነው ዕቅድ እንደማይሳካ በተግባር አሳይተነዋል ሲሉ የአፋር ክልላዊ መንግስ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ።
 
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ የአፋር ህዝብ የሀገሩን ዳር ድንበር በማስጠበቅ ለዘመናት አኩሪ ገድሎችን ሲፈጽም የኖረ ኩሩ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸባሪው ቡድን በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ለማቋቋም የሚያግዝ 150 ሚሊየን በጥሬ ገንዘብ እና 50 ሚሊየን የሚገመት በዓይነት ዛሬ አበርክቷል።
 
ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ ድጋፉን ከአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት÷አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን በማፍረስ ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የቆየ እቅዱን አፋርን በመወረር ለማሳካት ሞክሯል።
 
በዚህም በሌሊት በከባድ ጦር መሳሪያ የታገዘ የግፍ ጭፍጨፍ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ240 በላይ ንጹሃንን ዜጎች ላይ በመፈጸም የህዝብ ጠላትነቱን ማረጋገጡን ጠቅሰዋል።
 
አሸባሪው ቡድን በወረራው የሀገሪቱ ገቢና ወጪ ንግድ መስመርን ሚሌና የአዋሽ ላይ ለመዝጋት አልሞ ጦርነት ቢከፍትም በሀገሩና ክብሩ ፈጽሞ የማይደራደር የአፋር ህዝብ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ዕቅዱን ከንቱ ቅዠት አደርጎበታል ብለዋል።
 
ቡድኑ የአፋር ክልልን እንደመሸጋገሪያ ድልድይ ተጠቅሞ ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደማይቻል በሚገባው ቋንቋ በማናገር እንደማይሳካ በተግባር አሳይተነዋል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
 
አሸባሪው ቡድን በክልሉ በፈጸመው ወረራ ያደረሰውን ጉዳት በመረዳት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሀገሪቱን ገቢና ወጪ ንግድ መስመር በመዝጋት ህልውናችንን አደጋ ላይ ለመጣል የቃጣብንን ወረራ በመቀልበስ የአፋር ህዝብና መንግስት ታሪካዊ ሃላፊነቱን በሚያኮራ አግባብ ፈጽሟል ብለዋል።
 
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀደም ሲልም አሸባሪው ቡድን በአማራ ክልል በፈጸመው ወረራ የተጎዱትን ለማቋቋም እንዲያግዝ 385 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.