Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ወራሪ ኃይል በዋግኽምራ እየተደመሰሰ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪ ዘማቾች በሚወስዱት የተቀናጀ እርምጃ አሸባሪው ወራሪ ቡድን እየተደመሰሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በድሃና፣ በአምደወርቅ፣ በፃግብጂ፣ በዝቋላ፣ በሳህላ ሰየምት እና መሰል አካባቢዎች በተወሰደበት የተቀናጀ እርምጃ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡
የድሃና ወረዳ ሚሊሻዎች ለአሚኮ እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ አካባቢያቸውን ለመውረር ሙከራ አድርጎ ሙት እና ቁስለኛ ሆኖ ቀርቷል፤ ዛሬም እየተለበለበ ነው።
የፋኖ አባላት በበኩላቸው÷ አሸባሪውን ወራሪ ኃይል በገባበት ገብተው አይቀጡ ቅጣት እየቀጡት መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም በቅርቡ ለአማራ ሕዝብ የድል ብስራት እናበስራለን ብለዋል።
የዘመቻው አስተባባሪዎች በበኩላቸው÷ የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተቀብለው በግንባር የተገኙ ጀግኖች አኩሪ ድል እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገን ጦር እያደረገ የሚገኘው ድጋፍ ሠራዊቱ እንዲያሸንፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ ተስፋዬ ገብሬ ጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪ ዘማቾች በሚወስዱት የተቀናጀ እርምጃ የዋግ ሕዝብ ከርሃብ፣ ከስደት እና ከውርደት ነፃ እየወጣ ነው ብለዋል።
አያይዘውም አሸባሪው ወራሪ ኃይል ቆራጥ ሕዝብ ያላትን ትልቅ አገር የማፍረስ ሕልሙ ቅዠት እየሆነበት መሆኑን አስረድተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.