Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በጋሸና እና ቡርቃ አካባቢዎች በቆየባቸው ጊዜያት ከፍተኛ ግፍና በደል ፈጽሞብናል-ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን በጋሸና እና ቡርቃ አካባቢዎች በቆየባቸው ጊዜያት እያሰፈራራ በማስጨነቅ ከፍተኛ ግፍና በደል እንደፈጸመባቸው ነዋሪዎች ተናገሩ።
የጋሸና እና ቡርቃ ከተማ ነዋሪዎች በሰራዊቱ ተጋድሎ ከአሸባሪው ጭቆና በመላቀቅ ነጻ በመውጣታቸው የተሰማቸውን ደስታም እየገለጹ ነው።
 
ከጋሸና ከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ቄስ በሪሁን ከበደ÷ የአሸባሪው ቡድን አባላት ሰው ሆኖ ከተፈጠረ ፍጥረት የማይጠበቅ ዘግናኝ ግፍ፣ መከራና ስቃይ እንደፈጸሙባቸው ተናግረዋል።
 
እኛ ጠባችንና ጠላታችን ከብልጽግና አመራሮች እንጂ ከህብረተሰቡ አይደለም እያሉ አታለው ወደ ከተማችን ከገቡ በኋላ ህጻናት ሳይቀር መግደላቸውን፤ መድፈራቸውንና ንብረት መዝረፋቸውን ይገልጻሉ፡፡
 
የሌለንን የጦር መሳሪያ ደብቃችኋል፤ጉድጓድ ውስጥ ቀብራችኋል አምጡ በማለት ጠብ መንጃ ግንባራቸው ላይ በመደቀን ሲያስጨንቋቸው እንደቆዩ ቄስ በሪሁን አስታውሰዋል።
 
አሁን በጠቅላይ ሚኒስትራችን መሪነት በተጀመረው ማጥቃት ከፍተኛ ምት ደርሶባቸው ሲፈረጥጡ እንኳ ከጥፋታቸው አልማር ብለው ተጨማሪ ጥፋት እያደረሱ በዱር በገደሉ መግባታቸውን ጠቁመዋል።
 
በሰራዊቱ እልህ አስጨራሽ ትግል ከአራት ወራት ከጭቆና ተላቀን ነጻ በመውጣታችን በእጅጉ ተደስተናል ብለዋል ቄስ በሪሁን።
 
ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ መሬም መሃመድ በበኩላቸው÷ የሽብር ቡድኑ ለአቅመ ደካማና ለድሃ እንኳ የማያዝን ከፉ መሆኑን ነው የተናገሩት።
 
አቅመ ደካማ በመሆኔ አስፓልት መንገድ ዳር ሻይ ቡና እየሸጥሁ ቤተሰቤን ሳስተዳድር ብቆይም በሽብር ቡድኑ ምክንያት ስራ አቁሜ ለችግር ተዳርጌ ቆይቻለሁ ብለዋል፡፡
 
”አሁን ከተማችን ነፃ በመውጣቷ ስራ ጀምሬ ወደ ቀድሞ ህይወቴ ለመመለስ እየሞከርኩ ነው” ያሉት ወይዘሮ መሬም፤ ለቀጣይ ድል ሰራዊቱን በመደገፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
 
የህውሃት ወራሪና ዘራፊ ቡድን በመሬት ላይ እንዲኖር መፍቀድ ተጨማሪ ግፍ እንዲፈፅም እድል መስጠት በመሆኑ አሁን በተጀመረው አግባብ የጥፋት ሴራውን ማክሸፍ እንደሚገባም አመልክተዋል።
 
በተመሳሳይ ዝርፊያን፣ ውድመት እና ጥፋትን የዕለት ግብሩ ያደረገው አሸባሪው የህወሓት ወራሪ በወገን ጦር ተመቶ ከመውጣቱ በፊት ቡርቃ ከተማ ላይም የጭካኔ በትሩን አሳርፎባታል።
 
በከተማዋ የሚገኙ የግለሰብ ቤቶችን የከባድ መሳሪያ ምሽግ በማድረግ ለጥፋት ዓላማው እንደተጠቀመባቸው ሲወጣ አዝረክርኮ የተዋቸው የጥፋት አሻራዎቹ ምስክሮች ናቸው።
 
የሽብር ቡድኑ ወራሪ ኢትዮጵያን አፍርሶ ከንቱ ቅዠቱን የመመስረት ህልሙ በጀግኖቹ የቁርጥ ቀን ልጆቿ አኩሪ ተጋድሎ ኮስምኖ ከቡርቃ እና አካባቢዋ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ተጠራርጎ ወጥቷል።
 
በጸያፍ ግብር የተካኑት የሽብር ቡድኑ ወራሪዎች የገቡባት የቡርቃ ከተማ የሕዝብና የመንግስት ተቋማት፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ተዘርፈዋል፣ በቃጠሎ ወድመዋል።
 
የአካባቢው ምንጮች እንደሚገልጹት የሽብር ቡድኑ ወራሪ ለጥፋት ግብሩ ማርከሻ ይሆንለት ይመስል ያገኘውን ሁሉ ማውደም፣ መዝረፍና ማቃጠል ይቀናዋል።
 
በቡርቃም የዜጎች መገልገያ የሆኑ ጤና ጣቢያዎች፣ ትውልድ የሚታነጽባቸው ትምህርት ቤቶች፣ ሱቆችና ሌሎችም ተቋማትን በመዝረፍና በማቃጠል አውድሟቸዋል ነው ያሉት።
 
ከኢትዮጵያ ማህጸን የወጣውን ጡት ነካሽ የሽብር ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማጥፋት አገርና ሕዝብ እፎይታ የሚያገኙበት ወሳኝ ወቅት መድረሱንም ነው የተናገሩት።
 
የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ተመስገን ቢረሳው ለኢዜአ እንደገለጹት÷የሽብር ቡድኑ በህዝብ ላይ ግፍና ሰቆቃ በመፈጸም አረመኔንና አውሬነቱን በተግባር አረጋግጧል ፡፡
 
እድሜ ልኩን የኢትዮጵያ ህዝብ መዝረፉ፣ መግረፉና መግደሉ ሳይበቃው አሁንም ሀገርን ለመበታተን ቢጥርም የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ እየመከተው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ቡድኑ ጋሸና ላይ ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ የሰራው ምሽግም በቅንጅት ተሰብሮ ለከፍተኛ ኪሳራ በመዳረግ ከሞት የተረፈ ኃይሉ እግሩ እንደመራው እየፈረጠጠ ነው ብለዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.