Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሓት ቡድን የፈጸማቸውን ወንጀሎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማጋለጥ ይገባል – ሞርጋን አርቲዩኪና

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሃት ቡድን በፈጸማቸው ኢሰብዓዊ ድርጊቶችና አስጸያፊ ተግባራት ላይ ያተኮረ ዶክመንተሪዎች በመሥራት እና መሰል መረጃዎችን በማሰራጨት ወንጀሎቹን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማጋለጥ እንደሚገባ የስፑትኒክ እና የግሎባል ታይምስ ጸሐፊ ሞርጋን አርቲዩኪና ገለጸች፡፡
 
ተቀማጭነቷን አሜሪካ አድጋ ለስፑትኒክ እና ለግሎባል ታይምስ የምትጽፈው ሞርጋን አርቲዩኪና “ኒውዮርክ ታይምስ” እና “ሲ ኤን ኤን” ን ጨምሮ አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ ወንጀል የፈጸመ አሸባሪ ቡድን መሆኑን እያወቁ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ላይ መጠመዳቸውን አብራርታለች፡፡
 
ሞርጋን አርቲዩኪና ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በሰካይፒ ባደደገችው ቆይታ፥ የአሜሪካ መንግስት በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ሲፈልግ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ አመለካከት ለመቀየር አስቀድሞ እነዚህን መገናኛ ብዙኃን እንደሚጠቀምና ሴራውን ለማስፈጸም የሚረዱትን አጀንዳዎች ቀርፆ መረጃዎችን እንደሚያሰራጭ ነው የገለጸችው፡፡
 
መገናኛ ብዙኃኑ በኢትዮጵያ ላይ እንደሚያሰራጩት የሃሰት ዘገባዎች ሁሉ እንደ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ቬንዙዌላ፣እና ሌሎች በርካታ የዓለም ሀገራት ላይ ሲያሰራጩ እንደነበረና መረጃዎቹን ተከትሎ አሜሪካ በሀገራቱ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ብሎም ሀገራቱን ለመውረር እንደበቃች ነው ያስታወሰችው፡፡
 
በሌላ በኩል እንደ ስፑትኒክ ያሉ መገናኛ ብዙኃን እውነትን ለመግለጥ እየሠሩ እንደሆነ ገልጻ፣ ለአብነትም የአሜሪካና የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ከህወሓት ሰዎች ጋር ጋር ያደረጉትን ሚስጢራዊ ውይይት ስፑትኒክ ሬዲዮ እንዳጋለጠ ጠቅሳለች፡፡
 
ሞርጋን አርቲዩኪና እንደምትለው÷ በቀጣይ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ምስክርነት እንዲሰጡ በማድረግ፣ አረመኔው ቡድን በፈጸማቸው ኢሰብዓዊ ድርጊቶችና አስጸያፊ ተግባራት ላይ ያተኮረ ዶክመንተሪ በመሥራት እና መሰል የመረጃ ማሰራጫዎችን በመጠቀም ወንጀሉን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትዊተር፣ በፌስ ቡክ እና በሌሎች የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ማጋለጥ ይገባል ብላለች፡፡
 
ጸሐፊዋ ÷ የ “በቃ” ንቅናቄ የምዕራባውያኑን እና የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃንን ያሳፈረ፣ ከአፍሪካ አልፎ ዓለም አቀፋዊ የነፃነት ንቅናቄ መሆን እንደቻለ ገልጻ፥ “ብቸኛ ውሳኔ ሰጪ” በሆኑ ምዕራባውያን ሀገራት ላይ ሳይቀር ተጽዕኖ በመፍጠር ላይ እንደሆነም ነው የምትገልጸው፡፡
 
በቀጣይም ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ የኢትዮጵያ ወዳጆች፥ ፍትህንን የሚደግፉ የዓለም ህዝቦች ሁሉ የበቃን ንቅናቄ እንዲደግፉ ገልጻ፥ የ “ በቃ” ዘመቻ እንዲቀጥልም ነው ያሳሰበችው፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.