Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ኃይል ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን ከአዲስ ዘመን -እብናት-አምደወርቅ የሚያገናኘውን የተከዜ ወንዝ ድልድይ አፈረሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ሕዝብ የባህል፣ የታሪክና የሃይማኖት መገለጫዎች እንዲሁም መሰረተ ልማቶች በማውደም የሚታወቀው አሸባሪው የትህነግ ቡድን የተከዜ ድልድይን በማፍረስ የአካባቢውን ማህበረሰብ ትስስር አቋርጧል፡፡
የአሸባሪው ትህነግ መሰረተ ልማቶችን የማውደም ዓላማ የአማራን ሕዝብ በኢኮኖሚ የማጎሳቆል አንድ አካል መሆኑ በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች ያደረሰው ውድመት ያሳያል ነው የተባለው፡፡
የተከዜ ወንዝ ላይ ያለውን ድልድይ ማፍረሱም ሕዝቡ እንዳይጠቀም ከማድረግ ባለፈ ዓለም ዓቀፍ የሽብር ቡድን መሆኑን በግልፅ ያሳየበት ነው መባሉን ከአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.