Fana: At a Speed of Life!

አቅመ ደካሞችን ከጎዳና ለማንሳት የጀመርነው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል- ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለያዩ መድረኮች የተበረከቱላቸውን የጋቢ ስጦታዎች ለአቅመ ደካምች በስጦታ አበረከቱ፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፒያሳ አካባቢ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እና በቤኒ መስጂድ በመገኘት በተለያዩ መድረኮች የተበረከተላቸውን የጋቢ ስጦታዎች መልስው በየጎዳናው እና ቤተ እምነቱ ዙሪያ ለወደቁ፣ ጠያቂ ላጡ፣ የአገር ባለዉለታዎች እና አቅመ ደካማ ለሆኑ ዜጎች ነዉ ያበረከቱት ።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ስጦታውን ባበረከቱበት ወቅት እንደገለፁት፥ የተለያዩ መድረኮች እና ፕሮጀክቶችን ስንመርቅ ህዝቡን ወክለው እኛን ለማበረታታት በሽልማት መልክ የሀገር ባህል መገለጫ የሆነዉን ፤ በአገር ልጆች እጅ የተፈተለዉን ጋቢ ያበረከታችሁልኝን ሁሉ አመሰግናለሁ ብለዋል።

እኔም በቅድሚያ መሸለም ላለባቸዉ ለሀገር ብዙ ለፍተዉ በየጎዳናው እና ቤተ እምነቱ ዙሪያ ለወደቁ፣ ጠያቂ ላጡ፣ የሃገር ባለዉለታዎች ፤ አቅመ ደካምች መሆናቸውን ለማሰብ ያህል እናንተን በመወከል ከክረምቱ ቁር እና ዝናብ እንዲታደጋቸዉ አበርክቻለሁ ብለዋል።

በቀጣይም እነዚህን የአገር ባለዉለታ የነበሩ ወገኖቻችንን የእናንተን አቅም አስተባብረን በዘላቂነት ህይወታቸውን ለመቀየር እና ክረምቱ ሳይገባ በፊት ከጎዳና ለማንሳት የጀመርነዉን ጥረት እና መደጋገፍ አጠናክረን እንቀጥል ሲሉ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ ማቅረባቸውን ከአስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.