Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለተሰንበት የ”ሞመንት ኦፍ ዘ መንዝ” አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ”ሞመንት ኦፍ ዘ መንዝ” አሸናፊ ሆነች፡፡
አትሌት ለተሰንበት ግደይ መስከረም 27፣2013 ዓ.ም ስፔን ቫሌንሺያ ተካሂዶ በነበረው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረወሰን ማሻሻሏን ተከትሎ የፈረንጆቹ ኦክቶበር ወሩ አሸናፊ ተብላለች፡፡
የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 14 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ማሻሻል ችላ ነበር፡፡
ከዚህ ቀደም ከ12 ዓመታት በፊት በ14 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ ከ15 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ ጥሩነሽ ዲባባ የርቀቱ ክብረ ወሰን ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.