Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም ክብረወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ለተሰንበት ግደይ 10ሺህ ሜትር የሴቶች አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች፡፡
ከሶስት ቀን በፊት በሲፈን ሀሰን የተመዘገበውን ሪከርድ በማሻሻል ሪከርድ ያስመዘገበቸው፡፡
29 ደቂቃ 6 ሰከንድ 82 ማክሮ ሰክንድ በሲፈን ሀሰን ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ29 ዲቂቃ 01 ሰከንድ 03 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ሪከርዱን ያሻሻለችው፡፡
በኔዘርላንድ  ሄንጌሎ በተደረገ ውድድር ነው አዲስ የዓለም ክብረወሰን ያስመዘገበችው::
ለተሰንበት ግደይ የ 5 ሺህ ሜትር የዓለም ሪከርድ በእጇ የሚገኝ ስሆን የ10 ሺህ ሜትሩንም በመድገም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኢንግሪድ ክሪስተንሰን እአአ ከ1986 እሰከ 1993 በኋላ የመጀመሪያዋ እትሌት አድርጓታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.