Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓመቱ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን ውስጥ ተካተተች

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒው አፍሪካ መፅሔት በፈረንጆቹ 2021 ተፅዕኖ ፈጣሪ ነበሩ ካላቸው 100 አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ተካተተች፡፡

በስፖርቱ ዘርፍ ከተመረጡ ተፅጽኖ ፈጣሪዎች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ቀዳሚ ስትሆን÷ መፅሔቱ የለተሰንበትን የተፅዕኖ ፈጣሪነት ታሪክ ሲጀምር ክብረ ወሰኖችን በቀላሉ የሰባበረች ሲል ገልጿታል።

ኢትዮጵያ ከአበበ ቢቂላ እስከ ቀነኒሳ በቀለ፣ ከብርሃኔ አደሬ እስከ ጥሩነሽ ዲባባ ጀግኗ ሯጮችን ያፈራች ሀገር ናት ይላል መፅሔቱ።

እነ ቀነኒሳ እና ጥሩነሽ ከሩጫው ዓለም ቀስ በቀስ እየወጡ ቢሆንም የ23 ዓመቷ ለተሰንበት ግደይ በእነሱ የድል ቦታ ተተክታለች ነው ያለው።

 

ለተሰንበት በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5 ሺህ ሜትር ክብረወሰን በ2020 ጥቅምት ወር በእጇ ስታስገባ ዓለም መደነቁን ፅፏል።

 

ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ደግሞ የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረወሰንን በእጇ ማስገባቷ ይታወሳል፡፡

ጥቅምት ወር ላይ ቫሌንሺያ ውስጥ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ለተሰንበት 1 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በመግባት የዓለምን የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በእጇ ማስገባቷ የሚታወስ ነው።

 

በዚህም የስፖርት ውድድር ዘጋቢዎች ለተሰንበት ወንዶችን መፎካከር የሚያስችል ድንቅ ብቃት አላት አስብሏቸዋል።

 

ኒው አፍሪካ መፅሔት በመጪዎቹ ዓመታት ሌሎች ክብረወሰኖችን በመሰባበር የዓለም የአትሌቲክስ ኮከብ የኢትዮጵያ የስፖርት አምባሳደር የመሆን እድሉ እጇ ላይ መሆኑን አትቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.