Fana: At a Speed of Life!

አቶ ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ ላይ መቃወሚያ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)አቶ ልደቱ አያሌው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ክስ ላይ መቃወሚያ አቀረቡ፡፡

የአቶ ልደቱ አያሌው ሁለት ጠበቆች ዛሬ ከሰዓት ባቀረቡት መቃወሚያ የጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ መሰረት እስከ አንድ ዓመት መገልገል ይቻላል፤ የመጠቀሚያ ጊዜ አለው ብለዋል።

ለዚህም በዚህ አዋጅ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢነት የለውም፤ ስለዚህ በዚህ አዋጅ ሊከሰሱ አይገባም ያለ ሲሆን፥ በሁለተኛ ደግሞ የተከሰሱበት አንቀፅ ከፍ ያለ ነው፤ ክሱ ላይም ብዛት ያለው የጦር መሳሪያ ተብሎ የተጠቀሰው ነገር ግን አንድ መሳሪያ ነው፤ ይህም ተገቢነት የለውም የሚል መቃወሚያቸውን አቅርበዋል፡፡

ካላቸው የጤና ሁኔታም በውጭ ሀገር መታከም እንደሚገባቸው እና ዋስትና እንዲሚያስፈጋቸውም አቅርበዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጠው የአዳማ ከተማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ በአዋጁ የተሰጠው ህግ ወጥ የጦር መሳሪያ ሳይሆን በአንድ ዓመት ውስጥ መሳሪያ ያለው ሰው እንዲስመዘግብ ለማስቻል ነው፤ ይህም የሃገሪቱን ሰፋት ከግምት ውስጥ አስገብቶ እንጂ ህገ ወጥ መሳሪያ ይዞ እንዲቀመጥ አይደለም የተተረጎመው ፤ በዚህ መልኩ አንድ ዓመት ሙሉ የጦር መሳሪያ መታጠቅ አይቻልም ያለ ሲሆን፥ በአዋጁ አንቀፅ ስድስትም ቢሆን ሌላ የጦር መሳሪያ ፍቃድ እያላቸው ሁለተኛ መያዝ አይቻልም ብሏል።

እንዲሁም በሌላ ሰው ስም ተመዘገበ ሽጉጥ መያዝ አይችሉም፣ ሽጉጡም በሌላ ሰው ስም የወጣ ነው ያለው አቃቤ ህግ፥ የጤናቸውን ሁኔታ በሃገር ውስጥ ህክምና ያገኙ በመሆኑ የህክምና ክትትል ስለከሆነ ወደ ውጪ ሃገር የሚወጡት በዛው ወጥተው ሊቀሩ ስለሚችሉ ለዚህም ማረጋገጫ የለም ሲል ተቃውሞ ተከራክሯል፡፡

የሁለቱን ክርክር ያዳመጠው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለመስከረም 12 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.