Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከአለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከአለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር እስቴቨን ዌሬ ኦማሞ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ የክልሉ መንግስት በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ለመቆጣጠርና በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በጀት በመመደብ ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የውሀና የእንስሳት መኖ እያቀረበ እንደሚገኝ አቶ ሙስጠፌ ገልፀዋል።
ክልሉ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች በራሱ አቅም ምላሽ እየሰጠ ቢሆንም የምግብና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ለዚህም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ በበኩላቸው በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ በቀጣይ ለክልሉ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
በክልሉ የተከሰተው ድርቅ እያስከተለ የሚገኘው ችግር መገንዘባቸውን የገለፁት ተወካዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ በክልሉ ያለውን ችግር ለሎችም አጋር ድርጅቶች በማስረዳትና ሀብት በማሰባሰብ በክልሉ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድና በክልሉ መንግስት በሳል አመራር የጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የሚታየውን ሁለተናዊ ለውጥን ማድነቃቸውን የሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.