Fana: At a Speed of Life!

አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በወንጀል የተጠረጠሩ 20 የህወሃት ቡድን አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በዛሬው እለት የቀረቡት የህወሃት ቁልፍ አመራር ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ እና ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ይገኙበታል።
ተጠርጣሪዎቹ በሰሜን እዝ ላይ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት እንዲሁም ሌሎች ተደራራቢ የወንጀል ተግባራት የሚፈለጉ መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።
መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።
ፖሊስ በጠየቀው መሰረትም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.