Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመመረቅ ሮቤ ከተማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመንግስት፣ በሕዝብ እና አጋር አካላት የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ሥራ ለማስጀመር ሮቤ ገብተዋል፡፡
ከርዕሰ መተዳድር አቶ ሽመልስ ጋር የተባባሩት አረብ ኤምሬቶች ዓለም አቀፍ ቀይ ጨረቃ እርዳታ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ ፈህድ አብዱራህማን ቢን ሱልጣን እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በሮቤ ከተማ የተገነባው የኦሮሞ አርሶ አደሮች ትግል መሪ ጀኔራል ዎቆ ጉቱ ሃውልት የያዘው አደባባይ ዛሬ በርዕሰ መስተዳድሩ ከሚመረቁት ውስጥ ይገኝበታል።
ጀኔራል ዎቆ ጉቱ ሰላማዊ ትግል ተግባራዊ በማድረግ ከአምራቹ የባሌ አርሶ አደር የሚሰበሰብ ከፍተኛ ግብር ቢኖርም÷ በአካባቢው ምንም አይነት የልማት ስራ ተግባራዊ አለመደረጉን ተከትሎ ትክክለኛ ጥያቄ አንግበው የተነሱ የባሌ አርሶ አደር የትግል መሪ ናቸው።
ባለፉት ዓመታት ለበርካታ ጊዜ የባሌ ሕዝብ ጀኔራል ዎቆ ጉቱን የሚዘክር ሐውልት እንዲሠራ ጥያቄ ቢያቀርብም÷ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ዛሬ በ21ሚሊየን ብር የተገነባው ሐውልት የያዘው አደባባይ ይመረቃል።

ከዚህም በተጨማሪ የባሌ ዞን አስተዳደር ሕንጻ፣ አራት ትምህርት ቤቶች፣ የእናቶች እና ሕጻናት የህክምና ማዕከልን ጨምሮ÷ በ200 ሚሊየን ብር ወጭ የተገነቡ ስድስት የልማት ፕሮጀክቶች በርዕሰ መስተዳድር ሽመልሰ አብዲሳ እንደሚመረቁ ይጠበቃል።

በበላይ ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.