Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የገጠር ቤቶችን ወደ ዘመናዊ ደረጃ ለመቀየር የተነደፈውን ፕሮግራም አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ገጠር ቤቶችን ወደ ዘመናዊ ደረጃ ለመቀየር የተነደፈው ፕሮግራም ትግበራ ዛሬ አስጀምረዋል፡፡

በዚህም የኦሮሚያ ገጠር ቤቶች ግንባታ ማሻሻያ አዋጅ በሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ ቦሶቄ ተጀምሯል፡፡

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠሩን ህይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር አዳዲስ የማሻሻያ እርምጃዎች ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፥ ከነዚህ መካከል የገጠር ቤቶችን በአዲስ መልክ የተቀመጡ ደረጃዎችን አሟልተው እንዲገነቡ በማድረግ የቤተሰብ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተነደፈው ፕሮግራም በዛሬው ዕለት መተግበር ጀምሯል ተብሏል።

የክልሉ መንግሥት ቀደም ሲል የክልሉን ሽግግር ያፋጥናሉ ያላቸውን ሰባት ያህል አዳዲስ እርምጃዎች አውጆ እየተገበረ መሆኑን ከኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የገጠር ቤቶች ግንባታ ሽግግር አካል ለሆኑ የገጠር ቤቶች ኢንተርፕራይዞች የቡሉኬት ማምረቻ ማሽኖች የማስተላለፍ ስነስርዓት ተካሂዷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.