Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ልዩ መልእክተኛ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማርዲያት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የጋራ የልማት ፕሮጀክቶችን ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቢያትሪስ ካህሚሳ ዋኒ በሰጡት መግለጫ፥ በውይይቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማብራሪያ መስጠታቸውንና አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ገልፀዋል ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርም የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ጉዳዮችን እና የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የጋራ የልማት ፕሮጀክቶችን በበላይነት እንዲመሩ እና እንዲከታተሉ ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ለውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር እንዲሁም ለጆንግሊ ግዛት አስተዳዳሪ ሃላፊነት መስጠታቸውንም አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ አሁን ላይ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑን ያነሱት የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቢያትሪስ ካህሚሳ ዋኒ፥ ስለዚህ አሁን በጋራ ለመልማት የሚሰራበት ትክክለኛው ጊዜ ነው ብለዋል።
በውይይት ላይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በግላቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን በንግድ፣ በመሰረተ ልማት እና በኢኮኖሚ ለማስተሳሰር ከሀገራቱ መሪዎች ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ መግለፃቸውንም የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ አስታውቅዋል።
እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከፍ ላምደረግ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል ብለዋል።
ደቡብ ሱዳን የተረጋጋች ሀገር እንድትሆን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ላሳዩት አመራርነትም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አድናቆታቸውን መግለፃቸውንም የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትሩ በሰጠጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.