Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ተሻገር በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 3 ቤትና ንብረታቸው በእሳት የወደመባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ጎበኙ 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ትናንት በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ ጉዶባህር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ቤት ንብረታቸው በእሳት የወደመባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ጎበኙ፡፡

አቶ አገኘሁ ዘላቂ መፍትሄ በፍጥነት እንደሚሰጥና ለጊዜው አስፈላጊው የምግብና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ነው በጉብኝቱ ወቅት የገለጹት፡፡

በዛሬው ዕለትም የተለያዩ  የምግብና የተለያዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ለተጎጂዎች ቀርቧል፡፡

ርዕስ መስተዳድሩ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጋር መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት 62 ኩንታል ስንዴ፣ 31 ኩንታል መኮሮኒ፣ 250 እሽግ ፓስታ፣ 186 ሊትር ዘይት እና በአጠቃላይ  22 የሚሆኑ ዝርዝር ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ መስጠቱን የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ  ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ እያሱ መስፍን ገልፀዋል፡፡

በናትናኤል ጥጋቡ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.