Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በመልዕክታቸውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

“በዚህ ጊዜ የሃገራችንን ሉዓላዊነት አስጠብቆ ለማስቀጠል፤ የሰላም ዘብ ሆነን ለመዝለቅ እንዲሁም የተጋረጡብንን ፈተናዎች በድል ለመሻገር በፅናት ተደጋግፈን እና ተሳስበን በአንድነት የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን” ብለዋል በመልዕክታቸው።

በተለይ በየአካባቢው በተከሰቱ ግጭቶች እና ማንነትን መሰረት በማድረግ በተፈፀሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን ጠቅሰው፥ ለእነዚህ ወገኖች ትርጉም አዘል ድጋፍ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ህዝቡ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች በዕለት ደራሽ እና በመልሶ ማቋቋም የድጋፍ አግባብ በፍጥነት ለመድረስ በሃላፊነት ስሜት እንዲረባረብም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ፣ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እንዲሁም በሁሉም አካባቢዎች ፀጥታና ሰላም የማስፈን ተግባርም አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።

“በዓሉ በሚፈጥረው መልካም አጋጣሚ ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የሚነግስበት እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት የሚጠብቅበት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ”ም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.