Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤መስከረም 16፤ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከህንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብህራህማን ጃይሻንካር ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በታላቁ የህዳሴ ግድብ እና በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን÷ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ገንቢ ሃሳቦች ተለዋውጠዋል።

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ህንድ ያደረገችውን ድጋፍ አቶ ደመቀ አድንቀዋል።

አቶ ደመቀ በዚህ ወሳኝ ጊዜ በምክር ቤቱ ውስጥ ህንድ የነበራትን የፀና አቋም እና ድጋፍ በማመስገን፤ በሌሎች የጋራ ፍላጎቶች እና ጠቃሚ መስኮች ዙሪያ ቅንጅታችንን ማጠናከር ይገባናል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.