Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ እና በተመድ የሶማሊያ ተልዕኮ ኃላፊ ጄምስ ስዋን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች በቀጠናው ጉዳይ ላይ መረጃዎችን የተለዋወጡ ሲሆን በሶማልያ ጉዳይ ላይም መክረዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛውበሶማልያ የምርጫ ጉዳይ ዙሪያ ለአቶ ደመቀ ገለጻ ያደረጉላቸው ሲሆን

እንዲሁም ያሉትን ተስፋዎችንና ተግዳሮቶችን አንስተውላቸዋል፡፡

በተጨማሪም አልሻባብ በሀገሪቱ የደቀነውን የጸጥታ ስጋት እና ሌሎች ጉዳዮችንም አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው የሶማልያ የፌደራል መንግስት እያከናወነ ያለውን ጥረት አድንቀው ወደፊትም ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ጥረቶችን እንዲቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተው መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.