Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮችና ከሀገራቱ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮችና ከሀገራቱ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ከህብረቱ አምባሳደሮችና ከሃገራቱ ተወካዮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ነው የተመካከሩት፡፡

በውይይቱ ወቅት አቶ ደመቀ በትግራይ ክልል መንግስትና የዕርዳታ ድርጅቶች እያካሄዱት ስለሚገኘው ሰብዓዊ ጥረት አብራርተዋል፡፡

አክለውም መንግስት መድሃኒቶችን ጨምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ድጋፎችን በተለዩ 92 ማሰራጫ ጣቢያዎች ማዳረሱን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በክልሉ እየቀረበ በሚገኘው የሰብዓዊ ድጋፍ የመንግስት ተቋማት ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እና የዕርዳታ ድርጅቶች በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል፡፡

ከመልሶ ግንባታው በተጨማሪ የተቋረጡ አገልግሎቶችን ባንክ፣ መብራት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደ ስራ እየገቡ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደርም ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት በሁሉም አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ነው አቶ ደመቀ ያነሱት፡፡

በክልሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት አጋጥሟል ተብሎ የሚነሳው በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ሥራ መካሄድ ላይ መሆኑ ጠቁመው፣ የተጀመረው የማጣራት ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ችግር የፈጠሩ አካላት በጥንቃቄ ተለይተው ተጠያቂ ለማድረግ መንግሥት እንደሚሰራ አረጋግጠውላቸዋል።

በውይይታቸው ከትግራይ ክልል በተጨማሪ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስለምታከሄደው ጠቅላላ ምርጫ ለአምባሳደሮቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮችና የሀገራቱ ተወካዮች በበኩላቸው አሳሳቢ ነው ባሉት ጉዳይ ላይ ገለጻ ስለተደረገላቸው አቶ ደመቀን አመስግነዋል፡፡

ውይይቱ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በቅርበት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.