Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዱዋሂር ዱልካማል ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ጉዳይ እና በሦስትዮሹ የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያተኮረ እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡

በዚሁ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኮሞሮስ ሕዝብና ፕሬዚዳንት የተላከ መልዕክትም ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቅርበዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት በመዳሰስ፤ በኢንዱስትሪ ፣ በባህል እንዲሁም በህክምና ዘርፍ በተለይም የኮሮና በሽታን በጋራ ለመከላከል በጋራ ለመሥራት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኮሞሮስ ዜጎች ተመራጭ መሆኑንና ግንባር ቀደም አገልግሎት ሰጭ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ከሱዳን ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሀገራቸው ድርድሩ በውይይት እንደሚፈታም ታምናለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት በማስታወስ ፤ ግንኙነቱ የበለጠ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በኮሞሮስ በኩል ትብብር እንዲደረግባቸው ለቀረቡ መስኮች በጥናት ታይተው የሚመለሱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ኮሞሮስ የሦስትዮሹ ድርድር በውይይት እንዲፈታ ላሳየችው ተነሳሽነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

ለአፍሪካ ችግር አፍሪካ መፍትሔ ከሚለው መርህ በተቃራኒ የግድቡን ጉዳይ ፖለቲካዊና ዓለም አቀፋዊ መልክ እንዲኖረው እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ አስገንዝበዋል::

ኢትዮጵያ አሁንም ቢሆን በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት እየተመራ ያለውን የድርድር ሂደት እንደምትደግፍ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ቢሮ ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ እያደረገ ያለን ጥረት እንደሚያደንቁ የገለጹት አቶ ደመቀ በበርካታ መድረኮች ላይ ኮሞሮስ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም አጋርነት በማሳየትዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.