Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።
የሁለቱ ሀገራት ሚኒስትሮች ሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታላይ ተወያይተዋል።
የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል በሚሳተፉበት በሶማሊያ በሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አሚሶም) የትብብር ጉዳዮች ላይም መወያየታቸው ነው የተመለከተው።
የኢትዮጵያ መንግስት፥ ህወሓት ከሽብር ተግባሩ እንዲታቀብ እና የቀረበለትን የሠላም ጥሪ እንዲቀበል ከፍተኛ ጥረት ማድረጉንም አቶ ደመቀ መኮንን በዝርዝር ማስረዳታቸው ተጠቁሟል፡፡
መንግስት ለሠላም ባለው ትልቅ ቦታ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ እንዳይገባ መወሰኑንም ነው ያብራሩት።
በተጨማሪም መንግስት እስረኞችን ለመፍታት የወሰደውን የክስ ማቋረጥ እርምጃ ጠቅሰው፥ ሀገራዊ መግባባት ባልተደረሰባቸው ብሔራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ምክክር ለማካሄድ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅቶች መካሄዱን ለሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል።
ምንም አንኳ መንግስት ከእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለትግራይ ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊውን ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ቢሆንም፥ የሽብር ቡድኑ ግን በቅርቡ በአፋር ክልል በአባላ በኩል አዲስ ጥቃት በመክፈት የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ እንዲቋረጥ ማድረጉንም ገልጸዋል።
ይህም ቡድኑ ለትግራይ ህዝብ ደንታ የሌለው ሃይል መሆኑን እንደሚያመላክት ነው አቶ ደመቀ ያስረዱት።
ሶማሊያ በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን በሚመለከት ትክክኛ አቋም በማራመዷ ምስጋናቸውን ገልጸውላቸዋል።
ሚኒስትር አብዲሳኢድ ሙሴ አሊ በበኩላቸው ፥ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ለተሰጣቸው ዝርዝር ማብራሪያ አመስግነው ፥ ቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ሁሉን አቀፍ ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.