Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ተያያዝ ጉዳዮች ላይ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በሱዳንና ደቡብ ሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሆኑት አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ የተመራ ልዑክ ጋር መክረዋል።

አቶ ደመቀ ለልዑካን ቡድኑ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክተው ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአባይ ወንዝ 86 በመቶ ውሃ የሚታበረክት አገር መሆኗዋንና 60 በመቶ የሚሆኑ ዜጎችዋ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለማግኘት በጨለማ ውስጥ የሚኖር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ግድቡ በጨለማ የሚኖር ህዝቧን ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ ፕሮጄክት መሆኑን ነው አቶ ደመቀ የገለፁት፡፡

የአባይ ውሃን በፍትሃዊና እኩልነት መርህ  ለልማት ማዋል የኢትዮጵያ ህጋዊና ሉዓላዊ መብት መሆኑን አስረድተው፤ ኢትዮጵያ

ታችኞቹን የአባይ ተፋሰስ አገራትን የመጉዳት ምንም ፍላጎት እንደሌላት አቶ ደመቀ  ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል።

በሱዳንና በግብጽ በኩል የሚነሱ ስጋቶች ለመፍታት የሶስትዮሽ ድርድር ሲካሄድ መቆየቱን በማስታወስ፤  የሚነሱ ጉዳዮች በድርድር መፍትሔ ያገኝ ዘንድ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ሳታቋርጥ ሲትሳተፍ እንደቆየች አብራርተዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት በዲሞክራቲክ ኮንጎ መሪነት የሚካሄደው ድርደር እንዲቀጥል የኢትዮጵ ፍላጎት መሆኑን በመጠቆም ፤ እየተካሄደ የሚገኘው የሶስትዮሽ ሂደት መለወጥ ካስፈለገም  ሶስቱ አገራት በፈረንጆቹ 2015 በተፈራረሙት የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት(DOP) መሰረት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የግድቡ ደህነት አስመልክቶ ሱዳን የጠየቀቻቸው መረጃዎችንም የተሰጣት መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ለጉዳዮ በድርድር እንዲፈታ ቁርጠኛ መሆንዋን ለልዑካኑ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

በግድቡ የውሃ ሙሌት የግንባታው አንድ አካል መሆኑን  ጠቅሰው፤ እንደ አሜሪካ ያሉ ወዳጅ አገሮች  የህዳሴ ድርድር እንዲሳካእና በአካባቢው ያሉ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እንዳይሻክር ለሚያደርጉት ጥረት አክብሮታቸውን  ገልጸዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር በትብበር ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን  አቶ ደመቀ  አረጋግጠዋል፡፡

በሁለቱም ወገን የነበረው ውይይት በመግባባት  ላይ  የተመሰረተ እና  ውጤታማ እንደነበረ ነው የተገለፀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.