Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከተሰናባቹ የአዘርባጃን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የስራ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁት የአዘርባጃን አምባሳዳር ኤልማን አብዱላዬቭ ሽኝት አደረጉ፡፡

አቶ ደመቀ አምባሳደር ኤልማን አብዱላዬቭ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የሁለትን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ላከናወኑት ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

አቶ ደመቀ መንግስት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር በትግራይ ክልል እያቀረበ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍን ጨምሮ በክልሉ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር  ኤልማን አብዱላዬቭ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በቱሪዝም ዘርፍ ለመተባበር የሚያስችላቸው የብዝሃ ባህል እሴት ባለቤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም አዘርባጅን ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ እና ትምህርት ዘርፎች ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአምባሳሩ በቀጣይ የስራ ጊዜያቸው መልካም ነገር እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.